በጋምቤላ ክልል አልፎ አልፎ እየተፈጠሩ በማህበረሰቡ መካከል መቃቃር በመፍጠር ወደ ግጭት የሚያመሩ አለመግባባቶችን በዘላቂነት ለመፍታት ህዝባዊ የዕርቅ ጉባዔ ተካሄደ።

በጋምቤላ ክልል አልፎ አልፎ እየተፈጠሩ በማህበረሰቡ መካከል መቃቃር በመፍጠር ወደ ግጭት የሚያመሩ አለመግባባቶችን በዘላቂነት ለመፍታት ህዝባዊ የዕርቅ ጉባዔ ተካሄደ።

ጉባዔው በክልሉ መንግሥት የተዘጋጀ ሲሆን፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎትን ጨምሮ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈውበታል።

መድረኩ በክልሉ ለዘመናት ተከባብረው በሚኖሩ ብሔሮችና ብሔረሰቦች መካከል የነበረውን መልካም ግንኙነት በማፅናት፣ ለግጭት ምክንያት የሚሆኑ ጉዳዮችን በበሳል ውይይት በዘላቂነት ለመፍታት መሠረት የሚጥል እንደሆነ ይታመናል።

ክልሉ በኢትዮጵያ ተጠልለው ከሚገኙ ስደተኞች ከፍተኛ ቁጥር የሚያስተናግድ እንደመሆኑ፣ በአካባቢው የሚሰፍን ዘላቂ ሠላም የስደተኞችንም ደኅንነት በማስጠበቅ ረገድ ትልቅ ሚና ይኖረዋል።