ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የካቲት 23/2018 ዓ.ም ለስደተኞች የኢፍጣር እራት ግብዣ አደረጉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የካቲት 23/2018 ዓ.ም ለስደተኞች የኢፍጣር እራት ግብዣ አደረጉ።

በረመዳን ምክንያት መሰባሰቡ ርኅራኄ፣ አንድነት እና ሰብዓዊነትን ከማንፀባረቅ ባለፈ ኢትዮጵያ ለአብሮነት ያላትን ጠንካራ ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል ዶ/ር ዐብይ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያና ህዝቦቿ በእንግዳ ተቀባይነት ያላቸውን ታሪካዊ ሚና አስታውሰው፣ ስደተኞችና ለአደጋ የተጋለጡ ማህበረሰቦችን መደገፍ ከሰብዓዊነት ባሻገር የሀገሪቱን ጠንካራ የአቃፊነት ባህል የሚያመላክት መሆኑን ገልፀዋል።

የወደፊት እጣ ፈንታን ለመወሰን፣ ይህ ዓይነቱ አብሮነት ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ዶ/ር ዐብይ አስረድተዋል፡፡

Share: