Search
Close this search box.

በኢትዮጵያ ያሉ የሶሪያና የየመን ስደተኞች ተገቢው ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነ ተገለጸ።

በኢትዮጵያ ያሉ የሶሪያና የየመን ስደተኞች ተገቢው ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነ ተገለጸ።

በአንድ ወቅት በሀገራችን ተጠልለው የሚገኙ የየመንና የሶሪያ ስደተኞች መንገድ ላይ ሲለምኑ ይታዩ ነበር፡፡ ይህን ክስተት ያየ ኢትዮጵያዊ ግማሹ አዝኗል፤ ቀሪው ደግሞ ለሀገር ደኅንነት “ችግር ሊፈጥር ይችል ይሆን” የሚል ስጋት አሳድሮበት ነበር፡፡ 

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳሬክተር አቶ ብሩህተስፋ ሙሉጌታ እነዚህ የሶሪያና የየመን ስደተኞች በቪዛ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ እንደሆኑና፣ የስደተኝንት ጥያቄ አቅርበው እንደ ነበር ጠቅሰው ነገር ግን ቪዛ አግኝተው ከመምጣተቸው ጋር ተያይዞ አመልካቾቹን እንደ ስደተኛለመቀበል የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ባለመኖሩ በልዩ ፖለቲካዊ ውሳኔ የተወሰኑትን ዕውቅና መስጠት እንደተቻለ ገልጸዋል፡፡

በአሁን ወቅት ከ3 ሺህ ያልበለጡ የመናውያንና ሶርያውያን ስደተኞች አዲስ አበባ ውስጥ እንዳሉ የገለጹት አቶ ብሩህተስፋ፣ እነዚህ ስደተኞች በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ እና በለሎች አካላት ድጋፍ እየተደረገላቸውና በራሳቸው የሥራ ዕድል ፈጥረው እራሳቸውን ችለው የሚገኙ በመሆኑ እንደቀድሞው በልመና ሲሳተፉ በብዛት እንደማይታዩ ተናግረዋል፡፡

እነዚህ ስደተኞቹ የጥፋት ኃይል እንዳይሆኑ የቁጥጥር ሥራው የኢትዮጵያን እንግዳ ተቀባይነት በማይጎዳ መልኩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አቶ ብሩህተስፋ ገልጸዋል፡፡

Share: