የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ለደባት ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት 8 ሚሊዮን ብር የሚገመት ዘመናዊ አንቡላንስ ድጋፍ አደረገ::

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት በእርዳታ ከተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽን የተገኘ ዘመናዊ አምቡላንስ መኪና ለዳባት ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በድጋፍ አበርክቶአል፡፡ በርክክቡም ወቅት የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የአለምዋጭ ሳይት አሰተባባሪ አቶ ታምራት ደምሴ ልገሳው በወረዳው የሚታየውን አምቡላንስ መኪና እጠረት እንድሚፈታ እና ድጋፉ የህብረተሰብ ጤና አገልግሎትን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግና የአካባቢውን ማህበረሰብና ኤርትራዊ ስደተኞችን ተጠቃሚ ልማድረግ ያለመ መሆኑን አሰረድተዋል፡፡

ኢትዮጲያዊ እጆች ለሰብዓዊነት!