Search
Close this search box.

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት ድጋፋዊ ሱፐርቪዝን አከናወነ

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት ድጋፋዊ ሱፐርቪዝን አከናወነ

በስደተኛ ምላሹ ያለውን አፈጻጸም ለመመልከትና ድጋፍ ለማድረግ ይቻል ዘንድ የድጋፍና ሱፐርቪን ቡድኖችን በማዋቀር በጋምቤላ፣ መልካዲዳ፣ ጂግጂጋ፣ አሶሳ እና ሠመራ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችና በሥራቸው በሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች ሠፊ የድጋፍና ክትትል ሥራዎች ተከናውነዋል።

በድጋፋዊ ሱፐርቪዢኑ በዋናነት በመደበኛ ሥራዎችና የፕሮጀክቶች ሽግግር ላይ ያተኮረ የመስክ ምልከታና ድጋፍ የተከናወነ ሲሆን የመልካም አስተዳደር ችግሮችና መፍትሄዎች ላይም ሠፊ ውይይት ተደርጓል።

ይህን ተከትሎ ሰኔ 1/2016 ዓ.ም የተቋሙ ክፍተኛ አመራርና የሚመለከታቸው የሥራ ክፍል ተጠሪዎችና የቡድን መሪዎች በተገኙበት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።

ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ያዕቆብ ያላ ሱፐርቪዥኑ የተከናወነው በአፈጻጸሞቻችን ላይ ያሉ ጠንካራ ጎኖችን አበርትቶ ለማስቀጠል፣ ክፍተቶችን ለመሙላትና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ድጋፍ ለማድረግ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መቅረፍን ዓላማ ባደረገ መልኩ እንደሆነ አስታውቀዋል።

ሪፖርቶቹን ተከትሎ የዘርፍ ተጠሪዎች በቀረቡ ግኝቶች ላይ ማብራሪያ አቅርበዋል።

በመርሃ-ግብሩ ማጠቃላያ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር፣ ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን በዚህ መልኩ የተሟላ እና ተልዕኳችንን ሊደግፍ የሚችል ሱፐርቪዥን መካሄዱ ትልቅ ስኬት ነው ሲሉ ገልጸዋል። በተጨማሪም የሱፐርቪዥን ቡድኑ ግኝቶቹን በየክፍሎቹ ለይቶ ቀጣይ ምላሾችን ተፈጻሚ ለማድረግ በሚያስችል መልኩ ለሚመለከታቸው ክፍሎች ተደራሽ እንዲያደርጉ፣ ይህን መነሻ በማድረግም ሁሉም የሥራ ክፍሎችና በየደረጃው ያሉ ኃላፊዎች ወደ ውስጥ በመመልከት የሚመለከቷቸውን ጉዳዮች እንዲወስዱና በአጭር ጊዜ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን እንዲያስቀምጡና ለተፈጻሚነታቸውም በቁርጠኝነት እንዲሠሩ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

Share: