Search
Close this search box.

እንቁጣጣሽ – መልካም አዲስ ዓመት!

እንቁጣጣሽ – መልካም አዲስ ዓመት!

የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት በልምላሜና አደይ አበባ የሚያሸበርቅበት፣ ለውጥን ከተስፋ ጋር የሚያስተሳስር የዘመን መለወጫ ወቅት ነው፡፡

ዘመን ሲለወጥ፣ ሰዎች ባለፈው አመት የነበሩ የሕይወት ውጣ ውረዶችን ዘግተው፣ አዲሱ ዓመት የሠላም፣ የስኬትና የልማት እንዲሆንላቸው በመመኘት ትልም ያስቀምጣሉ፡፡

የአዲስ ዓመት መባቻ ግለሰቦች ብቻ ሳይሆኑ ድርጅቶችና ተቋማትም ባለፈው ዓመት የነበሩ ክፍተቶችን ለመሙላት፣ ስኬቶችን ለማስቀጠልና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ከሠራተኞቻቸው፣ ከባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመምከር በአዲስ መንፈስ ለጋራ ስኬት ቃል ኪዳናቸውን የሚያድሱበት ወቅት ነው፡፡

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎትም በ2015 ዓ.ም የነበሩ ዓለም አቀፋዊና ሀገራዊ ፈተናዎችን በመቋቋም ከጎረቤት ሀገራት የመጡ አንድ ሚሊዮን ስደተኞችንና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ተቀብሎ በውስን ኃብት ተገቢውን ድጋፍ እንዲያገኙ እየሠራ ነበር። ለዚህም በየደረጃው የድርሻችሁን የተወጣችሁ የተቋማችን ሠራተኞች፣ አመራሮች፣ አጋሮችና ባለድርሻዎች በእጅጉ ላመሰግን እወዳለሁ፡፡

አዲሱ ዓመት የሠላም፣ የአብሮነት፣ የስኬትና የልማት ዘመን እንዲሆንልን ከልቤ እመኛለሁ!

ጠይባ ሀሰን

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር

መስከረም 2016 ዓ.ም

Share: