Search
Close this search box.

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በክልሉ አስተማማኝ ሠላም ለማረጋገጥ ከክልሉ መንግሥት ጋር በመተባበር ሰሞኑን የሠላም ጉባዔ አካሂዷል፡፡

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በክልሉ አስተማማኝ ሠላም ለማረጋገጥ ከክልሉ መንግሥት ጋር በመተባበር ሰሞኑን የሠላም ጉባዔ አካሂዷል፡፡ ጉባዔው በክልሉ የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር ተከትሎ የተካሄደ ነው፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ህዝቡ አንድነቱንና አብሮነቱን በማጠናከር ለዘላቂ ሠላምና ልማት እውን መሆን የበኩሉን ሚና መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ተከስቶ ለነበረው የፀጥታ መደፍረስ ተባባሪ አካላት ላይ ተገቢ ማጣራት በማድረግ አስተማሪ እርምጃ እንደሚወሰድም ጠቁመዋል፡፡

በጉባዔው የክልል እና ወረዳ አመራሮች፣ የወጣት አደረጃጀቶች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የስ.ተ.አ ቅርንጫፍ ጽ/ቤትና ስደተኛ መጠለያ ጣቢያ አመራሮች፣ የስደተኛ ተወካዮች እና አጋር አካላት ታድመዋል፤ በክልሉ ሠላም እንዲሰፍንና የህዝቦች አንድነት እንዲጎለብት አበክረው እንደሚሠሩም አረጋግጠዋል፡፡

Share: