Search
Close this search box.

በዳባት ሳይት ፅ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑ 1200 የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ለ2016 አ/ም የትምህርት ዘመን የሚያገለግል የደብተር እና እስኪሪብቶ እርዳታ ልገሳ አከናወነ፡፡

በዳባት የስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት ሳይት ፅ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ የገቢ አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑ 1200 የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ለ2016 አ/ም የትምህርት ዘመን የሚያገለግል የደብተር እና እስኪሪብቶ እርዳታ ልገሳ በዛሬው ዕለት 10/01/20216 ዳባት በሚገኘው ፅ/ቤቱ አከናወነ፡፡

በዳባት ወረዳና ዙሪያ በጭላ፤ ሽምብራውሃ እና ገብርኤል አካባቢ ለሚገኙ ሰባት(7) የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለሚማሩና በአካባቢው ለተጠለሉ ተፈናቃይ ተማሪዎች እንዲሁም 44 የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች በአጠቃላይ 1200 ተማሪዎች ግምቱ ወደ 600,000.00 ሺህ ብር የሚጠጋ የደብተርና እስኪሪብቶ እርዳታ በስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዳባት ሳይት ፅ/ቤት የሰብአዊ ድጋፍና ልማት ፕሮግራም ሃላፊ አቶ ኢሳያስ ዮራ በተገኙበት ልገሳ ተደርጎላቸዋል፡፡
አቶ በለጠ ካሳሁን የወረዳው ትምህርት ፅ/ቤት ትምህርት ልማት ስታቲስቲክ ትንተና ዕቅድ ዝግጅትና ሃብት ማፈላለግ ቡድን መሪ (በተለይ) ለ RRS Communications ተሌግራም ገፅ እንደገለፁት በዛሬው ዕለት 10/01/2016 ዓ/ም በስ/ተ/አ ዳባት ሳይት ፅ/ቤት የተደረገው ልገሳ በአካባቢው ተቸግረው ላሉ ተማሪዎች እፎይታ የሚሰጥ እና ከተቀባይ ማህበረሰቡም ጋር ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት የሚያጠናክርና ችግሩን በመጠኑም የሚቀርፍ በመሆኑ የተሰማቸውን ደስታ ሳይገልጹ አላለፉም፤በቀጣይም ከስ/ተ/አ ጋር ተባብሮ ለመስራት አጋጣሚው ጥሩ በር ከፋች እንደሆነ አመላክተዋል፡፡

Ethiopian Hands for Humanity

#ኢትዮጲያዊ እጆች ለሰብዓዊነት!

Share: