Search
Close this search box.

2ኛው ዓለም አቀፍ የስደተኞች መድረክ በስዊዘርላንድ እየተካሄደ ነው

2ኛው ዓለም አቀፍ የስደተኞች መድረክ በስዊዘርላንድ እየተካሄደ ነው

(ታህሣሥ 03/2016 ዓ.ም)

የኢትዮጵያ መንግሥት የስደተኞችና ተቀባይ ማህበረሰቦችን ጉዳይ አንግቦ ከተቀረው ዓለም ጋር ለመምከር በስደተኞች መድረክ ታድሟል።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ፣ ከ1ኛው የስደተኞች መድረክ ወዲህ የተከናወኑ ተግባራትን የተመለከተ ሪፖርት ያቀርባል፡፡

የስደተኛውንና ተቀባይ ማህበረሰብን ሕይወት ለማሻሻል በሚቀጥሉት አራት ዓመታት የሚተገበሩ አዲስ ቃል-ኪዳኖችም ይፋ እየሆኑ ነው፡፡

ዓለም አቀፍ የስደተኞች መድረክ በመሠረታዊነት አጋርነትና ትብብርን ለማጠናከር፣ መንግሥታትን፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን፣ የሲቪል ማህበረሰቦችን፣ የግል ዘርፉን እና ስደተኞችን የሚያሰባስብ ሁነት ነው፡፡

Share: