በሸደር የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ በፀሐይ የሚሠራ አነስተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ተመረቀ፡፡
በሶማሌ ክልል ሸደር የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ተመርቆ የተከፈተው 254 ኪሎ ዋት ኃይል የሚያመነጨው ጣቢያ፣ 14 ሺህ ስደተኞች እና 3 ሺህ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡
የኃይል ማመንጫ ጣቢያው ወደ ሥራ መግባት፣ የስደተኞችና ተቀባይ ማህበረሰቡን ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ትስስር እንደሚያጠናክር ይታመናል፡፡
በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ የፌደራል ፔትሮሊየም እና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰህረላ አብዱላሂን ጨምሮ የሶማሌ ክልል ኃላፊዎች፣ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ፕሮቴክሽን ዳይሬክተር አቶ ዳባ ለሜሳ፣ የለጋሽ ተቋማት ተወካዮች እና አጋሮች ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡