Search
Close this search box.

ተቋርጦ የነበረው የስደተኞች ምግብ አቅርቦት በተቋሙ አመራርና በመንግሥት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጥረት ዳግም ተጀመረ

(ስ.ተ.አ – አዲስ አበባ)

ተቋርጦ የነበረው የስደተኞች ምግብ አቅርቦት በተቋሙ አመራርና በመንግሥት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጥረት ዳግም ተጀመረ

(ስ.ተ.አ – አዲስ አበባ)

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት አመራርና የመንግሥት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጥረት ፍሬ በማፍራቱ ለወራት ተቋርጦ የነበረው የስደተኞች ምግብ አቅርቦት ተጀምሯል፡፡

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን በምግብ ዕደላ ዳግም መጀመርና ሌሎች ተቋማዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ለስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች አስተማማኝ ከለላና ጥበቃ መስጠት ተቋሙ በትኩረት የሚያከናውነው ተግባር መሆኑን በመግለጫቸው በአፅንዖት አስረድተዋል፡፡ ስደተኞች፣ ጥገኝነት ጠያቂዎችና ተቀባይ ማሕበረሰቦች የተሻለ ሕይወት እንዲመሩም ባለድርሻዎችን በማስተባበር እንሠራለን ብለዋል፡፡

በቅርቡ በስዊዘርላንድ፣ ጄኔቫ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽነር 74ኛው የሥራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ፣ የኢትዮጵያ ልዑክ ለተቀባይ ሀገራት የሚደረግ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ጫና እና ኃላፊነት የመጋራት መርህ በተጨባጭ እንዲጠናከር መጠየቁንም ወ/ሮ ጠይባ አብራርተዋል፡፡ በስደተኞች ጥበቃና ራስን መቻል ዙሪያ እየተሠሩ የሚገኙ ሥራዎች፣ በዘርፉ የተመዘገቡ ስኬቶች፣ ፈተናዎችና በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራትም መነሳታቸውን ተናግረዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኤጀንሲንና አጋሮችን ያመሰገኑት ዋና ዳይሬክተሯ፣ በቀጠናዊ ግጭት ወደ ሀገሪቱ የሚተሙ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ሁኔታን መስመር ለማስያዝ ኢትዮጵያ ከባድ ኃላፊነት እየተወጣች በመሆኑ፣ ለጉዳዩ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት የተቀናጀ የቀውስ ምላሽ እንደሚያሻ መነሳቱን አውስተዋል፡፡

ታህሳስ 2023 በጄኔቫ በሚካሄደው የስደተኞች ጉባኤ የኢትዮጵያን ሚና ለማጉላት፣ ተቋሙ ባለድርሻዎችና አጋሮችን በማስተባበር ቅንጅታዊ ዝግጅት እያደረገ መሆኑም በመግለጫው ተዳሷል፡፡

ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎችን የማስተናገድ ልምድን ማስቀጠል፣ በውስን ኃብት የተቸገሩ ሰዎችን የማቀፍና የማረጋጋት ሚናን ማጠናከር፣ አካታች የሕግ ማዕቀፍ በማውጣትና በመተግበር በዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ያተረፍነውን አድናቆት ማስቀጠል እና “በሰብዓዊነት” መርህ ልዩ ትኩረት ለሚያስፈልጋቸው አካላት የሚከናወኑ ሥራዎችን በተሻለ ኃላፊነት ማስተባበር የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ቀጣይ ትኩረት መሆኑን ዋና ዳይሬክተር ጠይባ ሐሰን አስምረውበታል፡፡

ኢትዮጵያዊ እጆች ለሰብዓዊነት!

Share: