Search
Close this search box.

ኢትዮጵያ ለስደተኞች አካታች የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት ዘረጋች፤ ትግበራው የሀገር አቀፍ አገልግሎቶች ተደራሽነትን ያሳድጋል።

ኢትዮጵያ ለስደተኞች አካታች የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት ዘረጋች፤ ትግበራው የሀገር አቀፍ አገልግሎቶች ተደራሽነትን ያሳድጋል።

የካቲት ፳፯፯፣ 2016፣ አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ መንግሥት በስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት (ስ.ተ.አ) አማካኝነት ከተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኤጀንሲ እና ከብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎችን በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት ለማካተት ተግባራዊ እርምጃ ጀምሯል።

መሠረታዊ አገልግሎቶችን ለስደተኞች የማመቻቸት ዓላማ ያለው “ፋይዳ” የተሰኘ ልዩ መለያ ቁጥር ዲጂታል መታወቂያ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚኖሩ ስደተኞች እየተሰጠ ነው።

ባዮሜትሪክ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም በስደተኛ መታወቂያ ካርዶች ላይ የሚታተመው “ፋይዳ” ቁጥር፣ ተደራራቢ ምዝገባ እንዳይኖርና ለስደተኞች ከአንድ በላይ መታወቂያ እንዳይሰጥ ያስችላል።

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን፡- “የዲጂታል መታወቂያ ለስደተኞች የመስጠት ጅምር፣ በሀገር አቀፍ ሥርዓታችን ውስጥ አካቶን ለማሳደግ ያለንን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ትልቅ እርምጃ ነው። ይህ ተነሳሽነት በ2023 ዓለም አቀፍ የስደተኞች መድረክ የኢትየጵያ መንግሥት ይፋ ካደረጋቸው ሁለት ቃል-ኪዳኖች ጋር የሚጣጣም ነው፡- ስደተኞችን በሀገር አቀፍ ሥርዓቶች ማካተት እና የሠነድ ተደራሽነትን ማሳደግ። በእርግጠኝነት፣ መታወቂያው ስደተኞች በመንግሥት አቅጣጫ የሚቀመጥባቸውን አገልግሎቶች እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።” ብለዋል።

የተ.መ.ድ ስደተኞች ኤጀንሲ የኢትዮጵያ ተወካይ አንድሪው ቦጎሪ እንዳሉት “ይህ አስደሳች ዜና ነው። ኢትዮጵያ ስደተኞችን የሚመለከቱ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን በተግባር እየተረጎመች እንደሆነ የሚያሳይ ነው። ይህ መልካም ጅምር ስደተኞች ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ የሚያግዝ ይሆናል።” የተ.መ.ድ ስደተኞች ኤጀንሲም ተመሳሳይ እርምጃዎች በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እንዲጀመሩ ያበረታታል።”

“ማንነት ተኮር መታወቂያ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት ቁልፍ በሆነበት በዚህ ጊዜ ፤ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለስደተኞች መታወቂያ ብቻ ሳይሆን አስፈላጊ አገልግሎቶችን ፣ ህጋዊ ዕውቅና እና ከሚኖሩበት ኅብረተሰብ ጋር መስተጋብር ለመፍጠር የሚያስችል መንገድ ነው። በዚህም መሰረት ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች ያካተቱ የዲጂታል መታወቂያ ስርዓቶችን በኅብረት መገንባት ይጠበቅብናል።” ዮዳሄ ዘሚካኤል፣ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ተናግረዋል።

ይህ ፋይዳ ቁጥር የታተመበት አዲስ የስደተኛ መታወቂያ (ፋይዳ ቁጥር የታተመበት) ስደተኞች እንደ ሲም ካርድ ለማውጣት፣ የጤና እንክብካቤ ለማግኘት ወይም የትምህርት ቤት ምዝገባ ለማድረግ እና የመሳሰሉ ቁልፍ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ያስችላቸዋል። በተጨማሪም የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ፤ የባንክ ሒሳብቦችን ለመክፈትና በፋይናንስ ግብይቶች ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ መሳተፍና ድንግዶቻቸውን እና ግብይታቸውን በመደበኛነት ማስመዝገብ እንዲችሉ ይጠቅማቸዋል ይረዳቸዋል። ይህም ለሀገሪቱ ለአካባቢው ኢኮኖሚ አውንታዊ አዎንታዊ አስተዋፅዖ ያደርጋል።

ይህ ተነሳሽነት “የፒንግ ፕሮጄክት” (PRIMES Interoperability Gateway) በሚል ርዕስ ይህ ተነሳሽነት ለአንድ ዓመት ያህል ሲሰራ ቆይቷል። የስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች የመረጃ ጥበቃ መብቶች መከበራቸውን በማረጋገጥ የስደተኞች እና የብሔራዊ መታወቂያ ቋቶች መገናኘታቸውን ለማረጋገጥ UNHCR፣ RRS እና NIPD የሶስትዮሽ የመረጃ መጋራት ስምምነት ተፈራርመዋል።

ፕሮጀክቱ በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው እንደመሆኑ፣ ኢትየጰያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጭምር በቅድሚያ ተግባራዊ ካረጉት ሀገራት መካከል ያስመድባታል። ይህም ሀገሪቱ ስደተኞችን በሀገር አቀፍ ሥርዓቷ በማካተት ፈር ቀዳጅ ያደርጋታል። ይህ ተነሳሽነት ኢትዮጵያ በ2023 ዓለም አቀፍ የስደተኞች መድረክ 814,000 ስደተኞችን ወደ ብሄራዊ መታወቂያ ሥርዓት ለማካተት ቃል የገባችውን የመተግበር ሂደት አካል ነው።

በስደተኞች ፍላጎት ላይ የተመሠረተው የፋይዳ መታወቂያ፣ ግቡ በመጀመሪያ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ 77, 000 ስደተኞችን ተጠቃሚ ማድረግ ሲሆን፣ በቀጣይ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ከደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራና ሱዳን የተፈናቀሉ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ማዳረስ ነዉ። ኢትዮጵያ ብዙ ስደተኛ በማስተናገድ ከአፍሪካ በሶስተኛ ደረጃ ትገኛለች።

ይህ ውጥን የዓለም ባንክ መታወቂያ ለልማት ፕሮጀክት (ID4D) አካል ሲሆን፣ ይህም የዲጂታል መታወቂያና የሲቪል ምዝገባ ሥርዓቶችን አካታችነት፣ ተግባራዊነትና አስተዳደርን ለማሻሻል ያለመ ነው።

Share: