Search
Close this search box.

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት አመራርና ሠራተኞች ጳጉሜ 1 – “የአገልግሎት ቀን”

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት አመራርና ሠራተኞች ጳጉሜ 1 – “የአገልግሎት ቀንን” አስመልክቶ በዋና መሥሪያ ቤት እና በጉለሌ ቅርንጫፍ የሥራ ጉብኝት እና የተጨማሪ ሰዓት አገልግሎት አከናወኑ

(ጳጉሜ 1/2015 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ)

የአገልግሎቱ ሠራተኞችና ኃላፊዎች “ኢትዮጵያን እናገልግል” በሚል መርህ ቀኑን እስከ ምሽት 1 ሰዓት ለስደተኞች አገልግሎት በመስጠት ያሳለፉ ሲሆን የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተሮች አቶ ሙሉዓለም ደስታ እና ብሩህተስፋ ሙሉጌታ በጉለሌ ቅርንጫፍ በመገኘት የሥራ ጉብኝት እና የአገልግሎት ድጋፍ አድርገዋል።

አመራረሮቹ ዕለቱን አገልግሎት በመስጠት ከማሳለፍ በተጨማሪ የተቋሙ ሠራተኞች ስደተኞችን በትጋት እንዲያገለግሉ እና ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡ አበረታትተዋል።

#ኢትዮጵያን_እናገልግል!

#ኢትዮጵያዊ_እጆች_ለሰብዓዊነት!

Share: