Search
Close this search box.

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አከበረ፡፡

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አከበረ፡፡

የአገልግሎት መ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን ቀኑ የሚከበረው ሴቶች ለዕኩልነት ያደረጉትን ተጋድሎ ለመዘከር ነው ብለዋል፡፡

ራሳችንን እያበቃን በሴቶች ላይ ጫና የሚያሳድሩ አሠራሮችን መታገል ይገባል ያሉት ወ/ሮ ጠይባ፣ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ሴቶችን ለማብቃት እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

“የሴቶች ቀን ታሪካዊ ዳራ” እና “ሴቶችን ማብቃት” ላይ ያተኮሩ ጽሑፎች በተቋሙ የሴቶችና ሕጻናት አገልግሎት ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

Share: