Search
Close this search box.

የኢትዮጵያ መንግሥት ልዑክ በዓለም ስደተኛ መድረክ ለማሳተፍ ዝግጅቱን አጠናቋል

የኢትዮጵያ መንግሥት ልዑክ በዓለም ስደተኛ መድረክ ለማሳተፍ ዝግጅቱን አጠናቋል

(ታህሳስ 02/2016 ዓ.ም – ጄኔቭ)

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የሚመራው የኢትዮጵያ ልዑክ፣ ረቡዕ ለሚጀምረው 2ኛው የዓለም ስደተኛ መድረክ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን ተናገሩ፡፡

በጉባዔው የሚጠበቀውን መንግሥታዊ ሚና ለመወጣት ከሚመለከታቸው ተቋማት የተውጣጣ ልዑክ፣ በሲውዘርላንድ ከተለያዩ አካላት ጋር የቅድመ ጉባዔ ውይይቶችን እያካሄደ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሯ ገልጠዋል፡፡

ዋናውን መድረክ ጨምሮ ጎን ለጎን በሚዘጋጁ ሁነቶች፣ ኢትዮጵያ የስደተኞችና ተቀባይ ማህበረሰብን ሕይወት ሊለውጡ የሚችሉ የትብብርና ድጋፍ አማራጮች ላይ እንደምታተኩር ይጠበቃል፡፡

ኢትዮጵያዊ እጆች ለሰብዓዊነት!

Share: