Search
Close this search box.

አቶ ደመቀ መኮንን ከመንግስታቱ ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽነር ጋር ተወያዩ

አቶ ደመቀ መኮንን ከመንግስታቱ ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽነር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 5 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዴ ጋር በጄኔቫ ተወያዩ ።

አቶ ደመቀ ከ1 ሚሊየን በላይ የውጭ ስደተኞች መኖሪያ የሆነችው ኢትዮጵያ የስደተኞችን ህይወት ለማሻሻል እና ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የሚያስችሉ ስድስት ቃል ኪዳኖችን በመፈፀም ላይ እንደምትገኝ ገልፀዋል።

የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም ፣ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ማሳደግ ፣ ትምህርት፣ ዲጂታል ኮሙኒኬሽንን ተደራሽ ማድረግ ከቃል ኪዳኖቹ መካከል የሚጠቀሱ ሲሆን ባለፉት አራት አመታት ስለነበራቸው አፈፃፀም ገለፃ አድርገውላቸዋል።

ስደተኞች እና ተቀባይ ማህበረሰብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻልም መንግስት ቃል ኪዳኖቹ ተፈፃሚ እንዲሆኑ በቁርጠኝነት መስራቱን ይቀጥለል ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዴ በበኩላቸው የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የረጅም አመታት አጋርነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

አቶ ደመቀ ትናንት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጉዳይ ልዩ አማካሪ ሮበርት ፒፐር ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።

በውይይታቸው ሁለቱ ወገኖች ተፈናቃዮችን ለመጠበቅ እና ለመርዳት እና ወደ አካባቢያቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ የበለጠ ለማሳደግ ተስማምተዋል።

Share: