Search
Close this search box.

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት በ2016 ዓ.ም በዋናነት ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረገ

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት በ2016 ዓ.ም በዋናነት ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረገ

(መስከረም 23/2016 ዓ.ም)

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት በዋና መ/ቤት ደረጃ በ2016 በጀት ዓመት አንኳር የትኩረት መስኮች ላይ ከፍተኛና መካከለኛ አመራር፣ የዋና መ/ቤት እና የፕሮጀክት ጽ/ቤት ሠራተኞች በተገኙበት ውይይት አድርጓል፡፡

በውይይቱ የበጀት ዓመቱ ዕቅድ መነሻዎች፣ የባለፈው ዓመት አፈጻጸም፣ ጥንካሬዎችና ተግዳሮቶች፣ ነባራዊ መልካም አጋጣሚዎች፣ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ሥጋቶችና የመፍትሔ አቅጣጫዎች ተዳስሰዋል፡፡

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን ተሳታፊዎች በግልፅ ሀሳባቸውን እንዲያነሱ በጠየቁት መሠረት ከአሠራር፣ ከመልካም አስተዳደር፣ ከደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ፍትሃዊነት፣ ወዘተ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተዋል፡፡

በውውይቱ የተነሱ ሃሳቦችን በግብዓትነት በመቀበል የአገልግሎቱ ከፍተኛ አመራር በተወሰኑት ላይ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥቷል። በተያያዘም የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን ጠንካራ ተቋም ለመገንባት ሁሉም የአገልግሎቱ ሠራተኞችና አመራር የሚጠበቅበትን ድርሻ መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ወ/ሮ ጠይባ ተቋሙ ዘርፈ-ብዙ ሀገራዊ ኃላፊነቶች ስላሉበት አሠራሮችን ማዘመን፣ ተገልጋይን በአግባቡ ማስተናገድ፣ ውስጣዊ የመረጃ ልውውጥን ማሻሻል እና በኃላፊነት መንፈስ መሥራት እንደሚገባም በአፅንዖት ገልፀዋል፡፡

Share: