Search
Close this search box.

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግት፣ የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም እና የተ.መ.ድ ስደተኞች ኤጀንሲ ‘የመረጃ ልውውጥ ስምምነት’ ተፈራረሙ

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግት፣ የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም እና የተ.መ.ድ ስደተኞች ኤጀንሲ ‘የመረጃ ልውውጥ ስምምነት’ ተፈራረሙ

(መስከረም 25/2016 ዓ.ም – አዲስ አበባ)

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት፣ የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም እና የተባበሩት መንግሥታት ስደተኞች ኤጀንሲ የኢትዮጵያ ቢሮ ለስደተኞች የዲጂታል መታወቂያ ለመስጠት የሚያስችል ‘የመረጃ ልውውጥ ስምምነት’ ተፈራረሙ፡፡

የስምምነቱ ዓላማ ስደተኞች እና የተፈናቀሉ ወገኖች መሠረታዊ አገልግሎቶችን በጥራትና በፍጥነት እንዲያገኙ ማስቻል ነው፡፡

በስምምነቱ ወቅት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን ኢትዮጵያ ለስደተኞች የተሻለ ከለላ የምትሰጥና ከዜጎቿ እኩል የምታስተናግድ ሀገር መሆኗን ገልፀው ስምምነቱ የመንግሥት ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ኤክዝኪውቲቭ ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ ዘሚካኤል ኢትዮጵያ ስደተኞችና የተፈናቀሉ ወገኖችን ጨምሮ ለ90 ሚሊዮን ሰዎች ዲጂታል መታወቂያ ለመስጠት ማቀዷን ይፋ አድርገዋል፡፡

የተ.መ.ድ ስደተኞች ኤጀንሲ የኢትዮጵያ ተጠሪ አንድሪው ቦጎሪ በበኩላቸው ስምምነቱ ለስደተኞች የተሻለ ከለላ ለመስጠት የሚያስችል ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን ጠቁመው ስምምነቱን ለመተግበር ኤጀንሲው ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በቅርበት እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን፣ የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ኤክዝኪውቲቭ ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ ዘሚካኤል እና የተ.መ.ድ ስደተኞች ኤጀንሲ የኢትዮጵያ ተጠሪ አንድሪው ቦጎሪ የሶስትዮሽ ስምምነቱን ተፈራርመዋል፡፡

Share: