የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሠላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ውይይት አደረገ፡፡

በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን ውይይቱ ለጋራ ተልዕኮ ግልፅ ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡ አገልግሎቱ ትልቅ ኃላፊነት የተጣለበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ፣ ለሥራው የሚያስፈልጉ የሕግ ማዕቀፎችን ለማዘጋጀትና ለመተግበር ከተወካዮች ምክር ቤት ጋር መሥራት ተገቢ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሯ አንስተዋል፡፡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሠላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ዲማ […]