በምስራቅ አፍሪካ በተለያዩ መስኮች የፖሊሲ ምላሽ መስጠት የሚያስችል የ1.5 ሚሊዮን ዩሮ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።
ፕሮጀክቱ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የተፈጥሮ ኃብት መራቆትና ግጭት ከስደት ጋር ያላቸውን ግንኙነት በማጥናት መፍትሄ አመላካች ፖሊሲ ማዘጋጀት ላይ ያተኮረ ነው።
በ2050 በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ፣ በተፈጥሮ ኃብት መራቆትና በግጭት ሳቢያ በምስራቅ አፍሪካ እስከ 10 ሚሊዮን ሰዎች መፈናቀል ሊገጥማቸው እንደሚችል ትንበያዎች ያመላክታሉ፤ ስለሆነም ፕሮጀክቱ ይህን ለመቀልበስና ለመቋቋም እንደሚረዳ
ይጠበቃል፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጀይሉ ኡመር እነዚህን ጉዳዮች ለመቅረፍ የአየር ንብረት ለውጥ መላመድን፣ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን ማስቀጠልና ዘላቂ የኃብት አያያዝን የሚያበረታታ ሥርዓት መዘርጋት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲውም እንደ አህጉር የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ በትምህርት፣ መፍትሔ አፍላቂ ጥናቶችን በማከናወንና በማህበረሰብ አገልግሎት እየሠራ ይገኛል ብለዋል።
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን እንደ አህጉር በተለያዩ ምክንያቶች የተሰደዱ ዜጎች መኖራቸውን አንስተው፣ ችግሩን ለመፍታት በማስረጃ ላይ የተመሠረተ ፖሊሲ ማዘጋጀትና ትብብርን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡
(ምንጭ:- የአ.አ.ዩ ፌስቡክ ገጽ | መጠነኛ አርትዖት የተደረገበት)







================
Join our social media platforms:
Facebook: @RRSEthiopia
Twitter (X)፡ @RRSEthiopia
Website: https://rrs.et/






