ኢትዮጵያ ስደተኞችን በማስተናገድ ያሳየችው ቁርጠኝነት የሚደነቅና ሊደገፍ የሚገባው መሆኑን የካናዳ፣ ጀርመን፣ ኦስትሪያ፣ ቤልጅየም፣ ኖርዌይ፣ ፊንላንድ እና ሉክዘምበርግ አምባሳደሮች ተናገሩ።

ኢትዮጵያ ስደተኞችን በማስተናገድ ያሳየችው ቁርጠኝነት የሚደነቅና ሊደገፍ የሚገባው መሆኑን የካናዳ፣ ጀርመን፣ ኦስትሪያ፣ ቤልጅየም፣ ኖርዌይ፣ ፊንላንድ እና ሉክዘምበርግ አምባሳደሮች ተናገሩ።

በስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የተመራው ልዑክ በጉብኝቱ ኢትዮጵያ ደቡብ ሱዳናውያንን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ስደተኞች በሠላም እንዲኖሩ የጎላ አስተዋፅዖ በማበርከቷ አመስግነዋል፡፡

መንግሥታቸው ለኢትዮጵያ ስደተኛ ኦፕሬሽን ድጋፍ ሲያደርግ እንደነበር የጠቀሱት አምባሳደሮቹ፣ በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የጋምቤላ ክልል በርካታ ስደተኞችን ማስጠለሉ የሚያስመሰግነው መሆኑን ጠቅሰው፣ ባለድርሻ አካላት በቂና ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ከዚህ አንጻር አምባሳደሮቹ በስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ያደረጉት ጉብኝት የድጋፉን አስፈላጊነት ለመገንዘብ መልካም አጋጣሚ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ክልሉ ለበርካታ ስደተኞች ከለላ ከመስጠት ባለፈ ያለውን ውስን ኃብት በማጋራት ጭምር ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው ባለድርሻ አካላት ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።