የፍልሰት መረጃ በሚያመነጩ ተቋማትና በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት መካከል የመግባቢያ ሥምምነት ፊርማ ተደረገ፡፡

የፍልሰት መረጃ በሚያመነጩ ተቋማትና በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት መካከል የፍልሰት መረጃን ለማጋራት የመግባቢያ ሥምምነትና ፕሮቶኮል ፊርማ ተደረገ፡፡ የሥምምነቱና ፕሮቶኮሉ መፈረም በሀገራችን የተበታተኑ፣ ተደራሽ ያልሆኑ፣ ያልተናበቡና የትንተና ሥራ ያልተከናወነባቸው መረጃዎችን ዘመኑ በሚጠይቀው አግባብ በማደራጀት ለሚፈለገው ጥቅም ለማዋል ይረዳል፡፡ እንዲሁም የፍልሰት መረጃን በአግባቡ ለማሰባሰብ፣ ለመተንተንና የብሔራዊ ፍልሰት ስታቲስቲክስ ለማመንጨት በተቋማት መካከል ቅንጅታዊ አሠራርን የሚፈጥር ነው፡፡ የመግባቢያ ሥምምነቱና ፕሮቶኮሉ […]