ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ተቋማዊ የሪፎርም ሥራዎችን አደነቁ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ተቋማዊ የሪፎርም ሥራዎችን አደነቁ፡፡
 
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት ጉለሌ በሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዋና መ/ቤት ጉብኝት አድርገዋል፡፡
 
አቶ ተመስገን በጉብኝታቸው ወቅት የተቋሙን የሪፎርም ሥራዎች፣ የሌማት ትሩፋት እንቅስቃሴዎች እና የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን ጎብኝተዋል፡፡
 
የተቋሙ አመራር፣ ሠራተኞችና ስደተኞች በኅብረት በዋና መሥሪያ ቤት፣ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችና በስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ያከናወኑት ተግባር፣ በውስጥ አቅም የተቋም ግንባታን እውን ማድረግ እንደሚቻል የሚያሳይ መልካም ተሞክሮ ነው ብለዋል።