እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ!
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት (ስተአ) መጽሐፍ አሳተመ።
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ “የስደተኛ መስተንግዶ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ የኢትዮጵያን አጠቃላይ ስደተኛ የማስተናገድ ባህልና ታሪክ እንዲሁም ተቋማዊ ጉዞ የሚያሳይ መጽሐፍ አዘጋጅቶ ለሕትመት ማብቃቱን በታላቅ ደስታ ያበስራል።
በሰባት ምዕራፎች የተቀነበበው መጽሐፍ፣ የኢትዮጵያን የረጅም ዘመን የስደተኞች አቀባበል ታሪክ፣ የተቋም አመሠራረትና አሠራር የሚዳስሱ ዋና ዋና ርዕሰ-ጉዳዮችን አካቷል።
በኢትዮጵያ የስደተኞች የሕግ ማዕቀፎች እና የዓለም አቀፍ ለውጦች፣ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች አመሠራረት እና ለስደተኞች የሚሰጡ መሠረታዊና ማህበራዊ አገልግሎቶችን የተመለከቱ ርዕሰ-ጉዳዮችም በመጽሐፉ ተዳስሰዋል።
ለስደተኞች የሚቀርቡ የዘላቂ መፍትሔ አማራጮች እና የፖሊሲ አቅጣጫዎች፣ ስደተኞችን ማስተናገድ የሚያስከትላቸው አዎንታዊ እና አሉታዊ ተፅዕኖዎች እንዲሁም ከስደት ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን ጉዳይም ተሠንዷል።
በተቋሙ የበላይ አመራር ክትትልና ድጋፍ፣ ከዋና መሥሪያ ቤት በተውጣጡ አዘጋጆች የተጠናቀረው መጽሐፍ፣ በቅርቡ በይፋ ተመርቆ ለአንባቢዎች፣ ለተመራማሪዎች ብሎም ለፖሊሲ አውጪዎች ትልቅ የመረጃ ምንጭ እንደሚሆን ይጠበቃል።
በድጋሚ እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ!









