የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ባርሃም ሳሊህ፣ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን እና የአጋር አካላት ተወካዮች በጋምቤላ ክልል ጉብኝት እያደረጉ ነው።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ባርሃም ሳሊህ፣ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን እና የአጋር አካላት ተወካዮች በጋምቤላ ክልል ጉብኝት እያደረጉ ነው።

ልዑኩ ጋምቤላ አየር ማረፊያ ሲደርስ፣ የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር ወ/ሮ ዓለሚቱ ኡሞድን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውለታል።

ልዑኩ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎችን በመጎብኘት ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በስደተኞች ወቅታዊ ሁኔታ እና ቀጣይ የትብብር ማዕቀፍ ዙሪያ ይመከራል።

ጉብኝቱ በክልሉ ለሚገኙ ስደተኞች እና ተቀባይ ማህበረሰቦች ዘላቂ መፍትሄዎችን ለማስፋፋት መልካም አጋጣሚ እንደሚፈጥር ይጠበቃል።

ምንጭ:- (የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት)