እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ!
ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን የ78ኛው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሊቀ መንበር ሆና ተመረጠች፡፡
በ77ኛው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዓመታዊ ስብሰባ፣ ኢትዮጵያ የ78ኛው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሊቀ መንበር ሆና ተመርጣለች፡፡
ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎችን የምታስተናግደው ኢትዮጵያ በኮሚሽኑ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሊቀ መንበርነት መመረጧ፣ ለስደተኞች ለምታደርገው ጥበቃና እንክብካቤ የተሰጣት ታሪካዊ ዕውቅና መሆኑን ልብ ይሏል፡፡
በድጋሚ እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ!
ኢትዮጵያዊ እጆች ለሰብዓዊነት!











