የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና በ2019 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ተወያየ፡፡

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና በ2019 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ተወያየ፡፡
 
በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት አንኳር አፈጻጸሞች፣ ያጋጠሙ ችግሮች እና የተወሰዱ መፍትሔዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
 
ዋና መሥሪያ ቤትን ጨምሮ በሁሉም የስደተኛ ኦፕሬሽኖች የነበሩ መልካም ተሞክሮዎች ተሠንደው መቅረባቸው እና የተሻለ አፈጻጸም ለነበራቸው ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች፣ የስደተኛ ማዕከላት፣ በየደረጃው ላሉ አመራርና ፈጻሚዎች ዕውቅና መሰጠቱ እንዲሁም ተቋሙ በውስጥ አቅም አዘጋጅቶ ያሳተመው “የስደተኛ መስተንግዶ በኢትዮጵያ” የተሰኘ መጽሐፍ መመረቁ መድረኩን ለየት አድርጎታል።
 
በተመሳሳይ ከአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ በጡረታ ለተሸኙ ባልደረቦችም የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።
 
በመድረኩ ማጠቃለያ አጋር ድርጅቶች ለስደተኞች እና ተቀባይ ማህበረሰቦች ገቢ ለሚያስገኙ ሥራዎች ትኩረት እንዲሰጡ ክትትል ማድረግ፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን ማስፋት እና ለዶክመንቴሽን ትኩረት መስጠት እንደሚገባ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን ተናገርዋል፡፡
 
የስደተኞች ተጠቃሚነትን የተመለከቱ የስኬት ታሪኮችን መሠነድ እና ማጋራት፣ የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን ማጠናከር እና የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ የመሳተፍ ባህልን ማዳበር እንደሚገባም ዋና ዳይሬክተሯ አሳስበዋል።
 
በሁነቱ ከዋና መ/ቤት፣ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችና ከስደተኛ መጠለያ ማዕከላት አመራሮች ታድመዋል።

Share: